ከአምናው 9ወር ጋር ሲነፃፀር የትራፊክ አደጋው መቀነሱ ተገለፀሲዳማ ክልል ሀዋሳ 2018 ዓ.ም የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ባለሙያዎች ድጋፍ፣ ክትትል እና መልከታ ለማድረግ በተገኙበት በመጀመሪያው ዕለት የሲዳማ ክልል የመንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊና የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊ ኮረኔል ሮዳሞ ኪአ በመክፈቻ ንግግራቸው ከአምናው 9ወር ጋር ሲነፃፀር የትራፊክ አደጋው መቀነሱ ገልፀዋል።ይህን ተከትሎም ከመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት የተወጣጡ ባለሙያዎች በተገኙበት ለመንገድ ደህንነት መረጋገጥ እና አስቸኳይ ህክምና መተግበር ይበልጥ አስተዋጽኦ ያላቸው የጤና ተቋም ፣የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ፣ የተሽከርካሪ ምርመራ ተቋማት እና በትምህርት ቤት የመንገድ ደህንነት ክባት ያሉበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ አከናውነዋል።በቀጣይ ቀናትም የአሽከርካሪዎች ስልጠና እና ሌሎች ተግባሮችም የሚከናወኑ ይሆናል።

June 16, 2024


1 Comment
Good