ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም አዳማ
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት በትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ስርዓት አፈፃፀም ላይ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ ።
የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ትዕግስቱ አምሳሉ በመክፈቻ ንግግራቸው የትራፊክ አደጋ በዓለም ብሎም በሀገራችን አሁንም በከፍተኛ ሁኔታ የዜጎችን ህይወት በመቅጠፍ እና ከፍተኛ የሆነ የሀገርን ኢኮኖሚ እያንገዳገደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ይህንን ችግር ለመፍታት የትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ስርዓት በማልማት ተግባራዊ ተደርጓል ብለዋል፡

ይህንን ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ ወጥና ተዓማኒ የሆነ ዘመናዊ የመረጃ ስርዓት መዘርጋታ እንደሚገባ ገልጸዋል::
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ረዳት ኮሚሽነር ሞገስ ቸኮል በበኩላቸው እንደገለፁት በዓለም ቀዳሚ የሆነውን የትራፊክ አደጋ መረጃ አሰባሰብ ስርዓት በሀገር አቀፉ ደረጃ ወጥ በማድረግ ተዓማኒ መረጃ መሰብሰብ እና መተንተን የሚያስችል ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
የትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ስርዓት አሰራርና አፈፃፀም ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ በአቶ አበራ እሸቱ የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት የአይ ሲቲ ስራ አሰፈፃሚ እንዲሁም ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮ/ር ጥላሁን ወ/ ትንሳዔ የትራፊክ እና ወንጀል ኢንተለጀንስ ጥናትና ትንተና መምሪያ ኃላፊ አቅርበዋል።
በመጨረሻም የትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ስርዓቱ ወደ ተግባር ያልገቡ ክፍለ ከተሞችና ክልሎች በፍጥነት ወደ ተግባር መግባት እንደሚገባ የስራ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ::

በውይይት መድረኩ የተሳተፉ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከ11ድ ክፍለ ከተሞች፣ ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ፣ ሸገር ሲቲ ፖሊስ ኮሚሽን ከ12ቱ ክፍለ ከተማ ኮሚሽነሮችና የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።


