+251 111 855 0783
info@rsifs.gov.et

Contact Us

Edit Template

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ሲስተምን (RDMS) ተረከበ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ጋር በጋራ ሲያበለፅጉት የቆዩትን የትራፊክ አደጋ መረጃ አስተዳደር ሥርዓት (Road Accident Data Management System – RDMS) በይፋ ተረክቧል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ርስቱ ይርዳው፣ የመረጃ ሥርዓቱን በተረከቡበት ወቅት ባደረጉት ንግግር ሲስተሙ በመላው ሀገራችን ለሚገኙ የፖሊስ ሠራዊት አባላትና የትራፊክ ደህንነት ባለሙያዎች ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃን ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።

ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል አክለውም የመረጃ ሥርዓቱ ከመተግበሩ በፊት ለዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን እንዲሁም የሙከራና የማስተዋወቅ ሥራዎች መሰራታቸውን አስታውሰዋል።

አሁን ላይ ሲስተሙ ወደ ሙሉ አቅም ትግበራ መግባቱን የገለፁት ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል የክልል ፖሊስ አመራሮችና የትራፊክ ዘርፍ ባለሙያዎች ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን በዳታቤዙ ውስጥ በማስገባት የተሟላ የመረጃ ሥርዓት እንዲገነባ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች፣ ባለንብረቶች፣ ኢንሹራንስ ሰጪዎችና ፖሊሲ አውጪዎች ወቅታዊና አስተማማኝ መረጃ የሚያገኙበት የመረጃ ሥርዓት መሆኑን የገለጹት ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አካላት በተደራጀና በተተነተነ መረጃ የትራፊክ አደጋ መንሥኤዎች ላይ ተመስርተው መረጃ መር ውሳኔዎችን በመስጠት የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ እርምጃዎችን እንዲወስዱ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

“ከአሁን በኋላ ትክክለኛ የትራፊክ መረጃዎችን ሌላ ሰው ሊነግረን አይገባም” ያሉት ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለመረጃ ሥርዓቱ ተግባራዊነት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ እና በዚህ ሥራ ላይ በማንኛውም ሁኔታ ወደ ኋላ የሚቀር ክልል ወይም አካባቢ ሊኖር አይገባም ሲሉ መመሪያ ሰጥተዋል።

ክቡር አቶ ጀማል አባሶ የመንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው አዲሱ የዲጂታል አሰራር ሥርዓት ከዚህ ቀደም ከወረዳ እስከ ፌደራል በወረቀት ይላኩ የነበሩ፣ ታማኝነት የጎደላቸውና ወጥ ያልሆኑ የሪፖርት መረጃዎችን ሙሉ በሙሉ በማስቀረት በሀገራችን የመንገድ ደህንነት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዳታ ላይ ተመስርቶ በጋራ ለመገምገምና ለመፍታት ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ አነስተኛ የተሽከርካሪ ቁጥር ያላት ቢሆንም ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ ከሚመዘገብባቸው ሀገራት ተርታ መሰለፏንና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) እና ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ጋር ወጥ በሆነ መረጃ ላይ አለመስማማት መኖሩን አንስተው ችግሩን ለመቅረፍ ሲስተሙን ዲጂታላይዝ ማድረግ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።

Previous Post

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Impact Financial

Good draw knew bred ham busy his hour. Ask agreed answer rather joy nature admire wisdom.

Latest Posts

Categories

Tags

Dedicated to reducing road crashes and providing reliable insurance fund services for a safer Ethiopia.

Services

Road Safety Awareness

Insurance Fund Service

Claims & Support

Public Reporting

Contact Info

© 2026 Road Safety and Insurance Fund Service